Home » News Events » ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ በራስ አቅም ሰብዓዊ ድጋፍን መሸፈን ለራስና ለአገር ክብር፣ ነጻነትና ሉዓላዊንት ዘብ መቆም መሆኑን የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ዶ/ር ሽፈራው ተ/ማሪያም ገለጹ፡፡

ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ በራስ አቅም ሰብዓዊ ድጋፍን መሸፈን ለራስና ለአገር ክብር፣ ነጻነትና ሉዓላዊንት ዘብ መቆም መሆኑን የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ዶ/ር ሽፈራው ተ/ማሪያም ገለጹ፡፡

ቀን፡- ሰኔ 17/2016 ዓ.ም

የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን አመራርና ሰራተኞች በሀገራዊ የማክሮ ኢኮኖሚ ዕቅድ የ10 ወራት አፈፃፀምና በኮሚሽኑ የዕቅድ አፈፃፀም ላይ ውይይት አደረገ።
የዕቅድ አፈፃፀሙን የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር የሆኑት ክቡር አቶ አይደሩስ ሀሰንና የኮሚሽኑ የስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈፃሚ በየተራ ያቀረቡ ሲሆን ውይይቱን የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ክቡር አምባሳደር ዶ/ር ሽፈራው ተ/ማሪያም አወያይተዋል።
ክቡር አምባሳደር ዶ/ር ሽፈራው ተ/ማርያም እንደተናገሩት በውይይቱ እንደተናገሩት ለዕለት ደራሽ የሚሆን ምርትና ምርታማትን በማሳደግ የሰብዓዊ ድጋፍ በራስ አቅም የሚለውን አስተሳሰብ በየደረጃው ካለው የመንግስት መዋቅር ጋር በመሆን እስከታች ድረስ ማስረጽ ላይ መስራት፣ ለቅጽበታዊ አደጋና ለሰብዓዊ ድጋፍ ለምላሽ የሚሆን በቂ ከምችት መያዝ፣ የተረጅ ልየታውን ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ በትክክል መስራት፣ ማህበረሰቦቻን የመረዳትና የመተጋገዝ ባህላቸው እንዲዳብር ማስቻል፣ የበጎ አድራጎት የሚሰሩ ሰዎችን ከሚመለከታቸው ጋር በመሆን በመስራት የቀጣይ ዕቅዳችን በትኩረትና ፈጠራ በታከለበት መንገድ በከፍተኛ ተነሳሽነት መንፈስ ለመስራት እራሳችንን ማዘጋጀት አለብን ብለዋል፡፡
ከዚህ ጋር በተያያዘ አምባሳደሩ ሰብዓዊ ድጋፍን ላልተገባ አላማ ለማዋል የሚደረገውን ርብርብ ሰራተኞቻን ከሚመለከታቸው የክልል መዋቅር ጋር በመቀናጀት ይህንን መቅረፍ ይገባናል ብለዋል፡፡
የአደጋ ስጋት አመራር ፖሊሲን በየደረጃ ያለ የመንግስት መዋቅር አውቆና ተረድቶ በትትክክ ተግባራዊ እንዲያደርግ መስራት ይገባል ለዚህም ኮሚሽናችን የማስረጹን ተግባርም ይወጣል ብለዋል፡፡ አሁን የተፈጠረው አገራዊ ንቅናቄ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የተረጅነት አስተሳሰብን በመቅረፍ በራስ አቅም ለዜጎቻን ምላሽ መስጠት የምንችልበት ቁመና ላይ ለመድረስ የምናደርገውን ርብርብ ክልሎች የከተማ አስተዳደሮች ንቅናቄውን ጀምረውታል፤ የኮሚሽናችን አመራሮችና ሰራተኞች ደግሞ ይህን በማገዝና በመደገፍ በየደረጃው በቁርጠኝነት እና በባለቤትነት መንፈስ እየተደጋገፍን እየተረዳዳን እስካለን ድረስ በጎ ነገርን ሰርተን ማለፍ አለብን ብለዋል፡፡
በመጨረሻም ክቡር አምባሳደር ዶ/ር ሽፈራው ተ/ማሪያም ያወያዩ ሲሆን ከተሳታፍዎች ለተነሱ አስተያየትና ጥያቄዎች ማብራሪያ በመስጠትና ቀጣይ አቅጣጫ በማስቀመጥ ውይይቱ ተጠናቋል ።
          
Monday, June 24, 2024