Home » News Events » በክቡር ም/ጠ/ሚ በአቶ ተመስገን ጥሩነህ ሰብሳቢነት የሚመራው የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ም/ቤት አስቸኳይ ስብሰባ በድሬዳዋ ከተማ አካሄደ።

በክቡር ም/ጠ/ሚ በአቶ ተመስገን ጥሩነህ ሰብሳቢነት የሚመራው የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ም/ቤት አስቸኳይ ስብሰባ በድሬዳዋ ከተማ አካሄደ።

ቀን፣ ነሃሴ 10/ 2016ዓ.ም ፡-የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ አካሄደ።

 

በክቡር ም/ጠ/ሚ በአቶ ተመስገን ጥሩነህ ሰብሳቢነት የሚመራው የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ም/ቤት አስቸኳይ ስብሰባ በድሬዳዋ ከተማ አካሄደ።

በም/ቤቱ ስብሰባ ላይ የክልል ፕሬዝዳንቶችና የከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች፥ የፌዴራል ሴክተር ተቋማት ሚኒስትሮች፥ የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ከፍተኛ አመራሮች፥ የክልልና የከተማ አስተዳደር የአደጋ ስጋት ኮሚሽነሮች ተገኝተዋል።

ም/ቤቱ ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች በራስ አቅም ድጋፍን ለማሟላት እስከ አሁን የደረሱበትን ደረጃ እና ወቅታዊ የሆኑ ዘርፈ ብዙ አደጋዎች ክስተትና የሰብዓዊ ድጋፍ አፈፃፀም ሪፖርት በም/ቤቱ ሴክረታሪያት በክቡር አምባሳደር ዶ/ር ሽፈራው ተ/ማርያም ቀርቧል።

የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ም/ቤት ሴክሬታሪያት ክቡር አምባሳደር ዶ/ር ሽፈራው ተ/ማርያም በሪፖርቱ እንዳቀረቡት ሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም ምላሽ መስጠት የአገራዊ ደህንነት ጉዳይ መሆኑን ጠቅሰው አያይዘውም የክብር፣ የነፃነትና የሉዓላዊነት ጉዳይ በመሆኑ ተናበን በትኩረት ልንሰራ ይገባል ብለዋል።

በተጨማሪም በኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ምክር ቤት የኢትዮጵያ ሜትሮሎጅ የባለፋት ጊዜያት አፈፃፀም ሪፖርትና የቀጣይ ጊዜ ዝግጅትን አስመልክቶ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ተሾመ ፈጠነ ለም/ቤቱ አቅርበዋል።

ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የተረጅን ቁጥር በተመለከተም ትክክለኛ መደጋገፍ የሚገባቸውን ዜጎች ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ በመለየት መደገፍ ያለባቸውን ብቻ መደገፍ አለባቸው የሚል መግባባት ተፈጥሮ ደጋግሞ በመከለስ የተረጅ ቁጥር ፈላጊዎችን መረጃ የማጥራት ስራ እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ፥ በድሬዳዋ ከተማ በተካሄደው የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ ላይ ያስቀመጧቸው 7 አበይት የመፍትሄ አቅጣጫዎች።

1 • ከተፈጥሮ አደጋ ውጪ ያሉ ተፈናቃይ ዜጎችን ወደ ነበሩበት በመመለስ፥ ለምርታማነት እና ማቋቋሚያ በሚሆን የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ መስራት።

2 • የተረጂዎችን እና ድጋፍ የሚሹ ዜጎችን የተጣራ መረጃ በመያዝ፥ የግል ማህደራቸውን በጥንቃቄ በመለየት አደራጅቶ ማስቀመጥ።

3 • ሀብትን በማሰባሰብ ረገድ ጥሩ አፈፃፀም ካሳዩ ክልሎች ተምክሮ በመቅሰም ተቀራራቢ የሆነ አፈፃፀም ላይ ለመድረስ መስራት።

4 • ቅፅበታዊ አደጋዎች ሊፈጠሩ እንደሚችሉ ታሳቢ በማድረግ ቅንጅታዊ ንቃተ ህሊና ይዞ መዘጋጀት እና የመሬት አጠቃቀምን በህግ ማዕቀፍ ማስተሳሰር፥ እንዲሁም በዝናብ ምክንያት ተጋላጭ የሆኑ አካባቢዎችን መለየት።

5 • በተፈጥሮ አደጋ ለተፈናቀሉ ዜጎች ዘላቂ የሆነ መፍትሄ በእቅድ ውስጥ በማስገባት፥ የአደጋውን ቀጥተኛ ተጎጂዎች በማዕቀፍ ውስጥ ማካተት።

6 • የመረዳዳት፣ የመደጋገፍ እና እርስ በእርስ የወንድማማችነት ባህልን ማጠናከር፤ እንዲሁም ክልሎች የያዙትን የመተሳሰብ እሴት አስቀጥለው በመጓዝ አብሮነታቸውን ማጠናከር።

7 • እቅዶችን በጊዜውና በወቅቱ በማጠናቀቅ የተጓተቱ እና የተንጠለጠሉ ስራዎችን መቅረፍ እንዲሁም በቀጣይ ከዝግጅት ምዕራፍ ጀምሮ በጠራ እቅድ ማከናወን።

                                                                                                                                                                 

Monday, August 19, 2024