Home » News Events » የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ከክልል የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽነሮች ጋር በመሆን የድረ-ገጽ (የበየነ መረብ) ውይይት በማድረግ “የሰብአዊ ድጋፍ በራስ አቅም“ ትግበራ ሂደት የደረሰበትን ደረጃ ገመገመ፡፡

የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ከክልል የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽነሮች ጋር በመሆን የድረ-ገጽ (የበየነ መረብ) ውይይት በማድረግ “የሰብአዊ ድጋፍ በራስ አቅም“ ትግበራ ሂደት የደረሰበትን ደረጃ ገመገመ፡፡

ቀን፡- ሰኔ 19/2016ዓ.ም

የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ከክልል የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽነሮች ጋር በመሆን የድረ-ገጽ (የበየነ መረብ) ውይይት በማድረግ “የሰብአዊ ድጋፍ በራስ አቅም“ ትግበራ ሂደት የደረሰበትን ደረጃ ገመገመ፡፡

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የሚመራው የአደጋ ስጋት ም/ቤት ፤ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ፖሊሲ መጽደቁን ተከትሎ “ከተረጂነት እንውጣ” የሚል አብዮት ቅስቀሳ ተጀምሮ ሁሉም የክልል ከፍተኛ መንግስታት እና የሁለቱ ከተማ አስተዳደር አመራሮች የሚመሩት ንቅናቄ ተፈጥሯል፡፡

ይህን መነሻ በማድረግ የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ዶ/ር ሽፈራው ተ/ማርያም ሰብሳቢነት እና የኮሚሽኑ ከፍተኛ አመራሮች “ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ሰብአዊ ድጋፍ በራስ አቅም ለመመለስ” የሚስችላቸውን የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ምን ደረጃ እንደደረሱ ለመስማትና የድጋፍና ክትትል ሥራዎችም ካሉ ለመደገፍ ያለመ (የበየነ መረብ) ውይይት የተደረገው፡፡

የክልል አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነሮችም የተረጂነትን አመለካከት መቀልበስ፤ ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ፤ ምግብና ምግብ ነክ ክምችቶችን ለመያዝና ለማጠናከር እያከናወኗቸው ያሉትን ተግባራት በዝርዝር በሪፖርታቸው ያቀረቡ ሲሆን አያይዘውም የገጠሟቸውን ተግዳሮቶችም እና ያሉትን ምቹ አጋታሚዎች አንስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ዶ/ር ሽፈራው ተ/ማርያም በውይይቱ እንደተናገሩት ክልሎች የተረጅነት እና የጠባቂነት አመለካከትን ለመቀልበስ በትኩረት መስራት እንዳለባቸው ገልጸው ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የጀመሯቸውን አበረታች ስራዎችንም አድንቀው ከዚህ ጎን ለጎንም የምግብና ምግብ ነክ ክምችቶቻቸውን ማሳደግ እንዳለባቸው በውይይቱ አንስተዋል፡፡ በተያያዘም ክቡር አምባሳደሩ እንደተናገሩት ይህን ለማድረግም የማጥራት የማቀናጀት እና የማሸጋገር ሥራ ላይ በትኩረትና በፍጥነት መስራት እንዳለባቸው አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡

      

Wednesday, June 26, 2024