Home » News Events » “ድርቁ ወደ ረሃብ እየተቀየረ ነው የሚለው ሃሳብ የተሳሳተ ድምዳሜ ነው”

“ድርቁ ወደ ረሃብ እየተቀየረ ነው የሚለው ሃሳብ የተሳሳተ ድምዳሜ ነው”

ጥር 9/2016 ዓ.ም

“ድርቁ ወደ ረሃብ እየተቀየረ ነው የሚለው ሃሳብ የተሳሳተ ድምዳሜ ነው”

አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም (ዶ/ር) የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር

***********************

በአንዳንድ አካላት ዘንድ በኢትዮጵያ ያለው ድርቅ ወደረሃብ እየተቀየረ ነው በሚል እየተሰነዘረ ያለው ሃሳብ የተሳሳተ ድምዳሜ ነው ሲሉ የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም (ዶ/ር) አስታወቁ፡፡ ሠብዓዊ ድጋፉን በራስ አቅም ከመቻል አልፎ ትርፍ አምራች እስከመሆን እንደሚሠራም ገልጸዋል፡፡

ኮሚሽኑ በቀጣይ ለስድስት ነጥብ ስድስት ሚሊዮን ዜጎች የሠብዓዊ ድጋፍ እንደሚቀርብ መግለጹ ይታወቃል።

ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው (ዶ/ር) ከሚዲያዎች ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ፤ በአንዳንድ አካላት ድርቁ ወደረሃብ ተቀይሯል ሲባል የሚነገረው ድምዳሜ የተሳሳተ ነው። በኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ስሌት ድርቁ ወደረሃብ አልተቀየረም።

ድርቁ ወደ ረሃብ እየተቀየረና ሰው እየሞተ ነው አይነት መደምደሚያ ላይ ለመድረስ የራሱ የሆነ ክትትል እና የራሱ የሆነ ማረጋገጫ መሥራትን የሚጠይቅ መሆኑን የጠቀሱት አምባሳደሩ፤ አንዳንድ አካላት በዚህ መንገድ የሚያናፍሱት እንዳልሆነ ተናግረዋል፡፡

Thursday, January 18, 2024