Home » About Us » Human Resources Directorate

Human Resources Directorate

 • ከኮሚሽኑ ዕቅድና በጀት በመነሳት የሥራ ክፍሉን ዕቅድና በጀት ያዘጋጃል፣ እቅድ አፈፃፀሙን እና በጀት አጠቃቀሙን በየወቅቱ ይከታተላል፤ ይገመግማል፤ ሪፖርት ያደርጋል፣ ቀጣይነት ባለው መልኩ የማሻሻያ ሀሳቦችን ያዘጋጃል፤ ይተገብራል፤
 • ዳይሬክቶሬቱን ይመራል፣ ያስተባብራል፣ ይቆጣጠራል፤
 • ከኮሚሽኑ ስትራቴጂያዊ እና ዓመታዊ ዕቅድ በመነሳት የሰው ኃብት ስትራቴጂያዊ ዕቅድ እና ዓመታዊ ዕቅድ ያዘጋጃል፤ የስራ ክፍሉን ይመራል፣ ያስተባብራል፣ ይቆጣጠራል፤
 • የሥራ ክፍሉን ተግባራት ለማከናወን የሚያስችሉ መመሪያዎችን ያዘጋጃል፤ ሲፀድቁም ተግባራዊ ያደርጋል፤
 • የመንግስት ሰራተኞችን አዋጅ በተከተለ አኳኋን የኮሚሽኑን የሰው ኃብት ሥራ አመራር ፖሊሲ፣ መመሪያዎች እና የሥራ ማኑዋሎችን በማዘጋጀት ወይም በማሻሻል ለበላይ ኃላፊው ያቀርባል፣ ሲፀድቁም ተግባራዊ ያደርጋል፤
 • የኮሚሽኑን ሰራተኞች የቅጥር፣ ምደባ፣ ዝውውር፣ ደረጃ እድገት፣ የሰው ሀብት ልማት፣ የእርከን ጭማሪ፣ የደመወዝ ማስተካከያዎችን እና ስንብት የመንግስት ሰራተኞች አዋጅና የኮሚሽኑ መመሪያ በሚያዘው መሠረት በአግባቡ ይፈጽማል፤
 • አዲስ ቅጥር ሰራተኞች ስለ መስሪያ ቤቱ አጠቃላይ ሁኔታ እና ስለተመደቡበት ስራ በቂ ግንዛቤ እንዲያገኙ ከሚመለከተው የስራ ክፍል ጋር በመነጋገር ስልጠና ያመቻቻል፣
 • ልዩ ልዩ የማበረታቻ ስርዓቶችን ይቀርፃል፤ ሲፀድቁም ተግባራዊ ያደርጋል፤ በኮሚሽኑ ውስጥ ምቹ የሥራ አከባቢን መፍጠር የሚያስችሉ ጥናቶችን በማጥናት ለበላይ ኃላፊው ያቀርባል፤ ሲፀድቁም ተግባራዊ ያደርጋል፤
 • የኮሚሽኑን ሰራተኞችና የሥራ ኃላፊዎች የዕቅድ አፈፃፀም ምዘና ውጤት ከሥራ ክፍሎች በማሰባሰብ ትክክለኛነቱን በማረጋገጥ ይይዛል፤ የምዘና ውጤቱንም በማጠናቀርና በመተንተን ለበላይ ኃላፊው ያቀርባል፤ ውሳኔ የሚሹ ጉዳዮች በሚኖሩበት ጊዜ ከበላይ ኃላፊው የሚሰጡ ውሳኔዎችን ተግባራዊ ያደርጋል፤
 • የኮሚሽኑን የሰው ኃብት ፍላጎት እና የብቃት ክፍተት በመፈተሽ እንዲሟላ ያደርጋል፤ ወይም የሚሟላበትን መንገድ ይቀይሳል፤
 • በመስሪያ ቤቱ ቅጥር ግቢ የሚገኙ ለጤና ጠንቅ የሆኑ ችግሮችን በዳሰሳ ጥናት በመለየት የመፍትሄ ሃሳቦችን ይጠቁማል'ለተፈፃሚነታቸው ክትትል ያደርጋል '
 • በኮሚሽኑ ውስጥ የሥራ ላይ ደህንነት ለሚያስፈልጋቸው ሰራተኞች በተቀመጠው ህግ መሠረት አስፈላጊውን ትጥቅና አበሎች ያሟላል፤ እንዲሟሉ ያደርጋል፤
 • በሥራ ክፍሉ የሚገኙ ሰራተኞችን አፈፃፀም በየወቅቱ ለማሻሻል የሥራ አፈፃፀም ምዘና ስርዓትን ተግባራዊ ያደርጋል፤
 • የዳይሬክቶሬቱን ዕቅድ አፈፃፀም በየወቅቱ ሪፖርት በማዘጋጀት ለዕቅድ፣ ለውጥና መልም አስተዳደር ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ያቀርባል፤ ይገመግማል፤ ያስገመልግማል፤ አፈፃፀሙ የማሻሻልበትን ዘዴ ይቀይሳል፤ ተግባራዊ ያደርጋል፤

Contact Info

ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ከንፋስ ስልክ የሙያ ትምህርት ቤት አጠገብ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ፣ ፖ.ሳ.ቁ  5686