Home » About Us » Internal Audit Directorate

Internal Audit Directorate

  • ቅድሚያ የሚሰጣቸው ተግባራትን ከመስሪያ ቤቱ ዓላማ ጋር የተጣጣሙ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ሥጋት/ተጋላጭነት ያለባቸውን የመስሪያ ቤቱን የስራ ክፍሎች መሰረት ያደረገ እቅድ ከሰው ሀይል አመዳደብ እና ከወጪ በጀት ፍላጎትጋር አጠቃሎ በማዘጋጀት ለመስሪያ ቤቱ የበላይ ኃላፊ አቅርቦ ማፀደቅና የኦዲት የስራ ትዕዛዝ እና ሃሳብ በመስጠት እቅድና ፕሮግራም ማዘጋጀት፣
  • የፀደቀውን እቅድ አዘጋጅቶ ለሚኒስትሩ ማቅረብ፣
  • የውስጥ ኦዲቱን መደበኛ የኦዲት እቅድ ሁሉም ኦዲት ተደራጊ የሥራ ክፍሎች እንዲያውቁ ማድረግ ፣
  • ኦዲተሮቹ ተለይተው የሚስጣቸውን የኦዲት ሥራ በብቃት ለማከናወን የሚያስችላቸው ዕውቀት፣ልምድ፣ክህሎትና ሌሎች ተፈላጊ ችሎታዎች እንዲኖራቸው የማድረግና የስልጠና ፍላጎቶችን በማቀድና በበላይ ኃላፊ በማጽደቅ አፈጻጸሙን መከታተል፣
  • የተዘረጋው የውስጥ ቁጥጥር ሥርዓት የመስሪያ ቤቱን ዓላማዎች በከፍተኛ ቁጠባና ውጤታማ በሆነ መንገድ ከግብ ለማድረስ ማስቻሉን በቂ መረጃዎችን ሰብስቦ በመገምገምና በቁጥጥር ስርአቱ ላይ ያለውን ስጋት ወይም ተጋላጭነት በመለየት ለመስሪያ ቤቱ የበላይ ኃላፊ ማሳወቅ፣
  • በፀደቀው እቅድ መሰረት የኦዲት መጀመሪያ ስብሰባ እና ኦዲቱን አከናውኖ የኦዲት ማጠናቀቂያ ስብሰባ ከሚመለከታቸው ሠራተኞች፣ የሥራ ኃላፊዎችና የመስሪያ ቤቱ የበላይ ኃላፊ ጋር ማድረግ፣
  • የተደረሰበትን ውጤት፣ ድምዳሜና የማሻሻያ ሃሳብ በሪፖርት ተገቢ ባህሪያት ላይ የተመሰረተ የተሟላ ሪፖርት አዘጋጅቶ ለመስሪያ ቤቱ የበላይ ኃላፊ ማቅረብ፣
  • አስቀድሞ በዕቅድ ያልተያዘ ልዩ ኦዲት እንዲያደርግ በመስሪያ ቤቱ የበላይ ኃላፊ ሲታዘዝ ኦዲት ማከናወን፣
  • በበጀት ዓመቱ መጨረሻ በመስሪያ ቤቱ አማካኝነት የተደረገውን ቆጠራ በፋይናንስ አስተዳደር አዋጅ፣ ደንብና መመሪያዎች መሰረት መከናወኑን በማረጋገጥ የቆጠራ ሪፖርቱን ከቆጠራ ሰነድ ጋር ለሚኒስቴሩ እንዲቀርብ የማድረግ፣ ይህንንም ለማረጋገጥ በቆጠራ ወቅት በታዛቢነት የመገኘት፣ በፈሰስ ሂሳብ ሥራ ላይ መሣተፍ፣
  • ቀድሞ በቀረቡት የኦዲት ሪፖርቶች መሠረት የእርምት እርምጃ ያልተወሰደባቸውን ግኝቶች በመከታተል የእርምት እርምጃ እንዲወሰድባቸው ለመስሪያ ቤቱ የበላይ ኃላፊ ማሳሰብ፣
  • የውጪ ኦዲተሮች በሚያቀርቧቸው ግኝቶች ላይ የእርምት እርምጃ እንዲወሰዱ ክትትል ማድረግ፣
  • በውስጥ ኦዲት የተከናወኑ ተግባራትን የሚገልጽ ወቅታዊና ዓመታዊ የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ለመስሪያ ቤቱ የበላይ ኃላፊ ያቀርባል፡፡

Contact Info

አድራሻ: ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ከንፋስ ስልክ የሙያ ትምህርት ቤት አጠገብ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ፖ.ሳ.ቁጥር 5686