Home » About Us » Legal Service

Legal Service

 • የኮሚሽኑን እቅድ መሠረት በማድረግ የሥራ ክፍሉን ዕቅድ ያዘጋጃል፤ የስራ ክፍሉን ይመራል፤ ያስተባብራል፤ ይቆጣጠራል፤
 • ኮሚሽኑ ከውጭ አካላት ጋር በሚያደርጋቸው ልዩ ልዩ ግንኙነቶችና የውል ስምምነቶች ላይ በመገኘት ከአገሪቱ ህግና ከኮሚሽኑ ጥቅም አንፃር ያለውን ፋይዳ ይገመግማል፣ በጉዳዩ ላይ የኮሚሽኑን ኃላፊ ያማክራል፤
 • ኮሚሽኑ ከሌሎች አካላት ጋር በሚያደረጋቸው የሥራ ግንኙነቶች እና እንቅስቃሴዎች አለመግባባት ቢፈጠርና ጉዳዩን በድርድር መፍታት በማይቻልበት ወቅት ኮሚሽኑን በመወከል በፍርድ ቤት ክስ ያቀርባል፤ ወይም ለቀረበው ክስ ምላሽ ይሰጣል፣ ይከራከራል፣ የፍርድ ውሳኔ ሲያገኝም ጉዳይን በመከታተል ያስፈፅማል፣
 • የህግ ጉዳዮችን በተመለከተ የኮሚሽኑ አማካሪ ሆኖ ይሰራል፤ ልዩ ልዩ ፖሊሲዎችና መመሪያዎችን ሲቀርፁም አስፈላጊውን የህግ ማማከር አገልግሎት ይሰጣል፣
 • ከኮሚሽኑ ተግባርና ኃላፊነት አንፃር የአገሪቱን ህጎችና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያገኙ የግዢ ስምምነቶችን ለኮሚሽኑ የሥራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች ግንዛቤ ያስጨብጣል፤ አሰራሩን ያማክራል፤
 • ለስራ ክፍሉ የሚያስፈልጉ የሰው ሀብትና ቋሚና አላቂ እቃዎች እንዲሁም ለስራ አስፈላጊ የሆኑ ሌሎች መገልገያ መሳሪያዎች እንዲሟሉ ያደርጋል፤
 • የለውጥ መሳሪያዎችን በሥራ ክፍሉ ተግባራዊ ያደርጋል፤
 • በሥራ ክፍሉ የሚገኙ ሰራተኞችን አፈፃፀም በየወቅቱ ለማሻሻል የሥራ አፈፃፀም ምዘና ስርዓትን ተግባራዊ ያደርጋል፤
 • ከሰው ኃብት ሥራ አመራር ዳይሬክቶሬት ጋር በመተባበር የዳይሬክቶሬቱ ሰራተኞችን አቅም የማጎልበት ስራ ይሰራል፤
 • የዳይሬክቶሬቱን ዕቅድ አፈፃፀም በየወቅቱ ሪፖርት በማዘጋጀት ለዕቅድ፣ ለውጥና መልም አስተዳደር ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ያቀርባል፤ ይገመግማል፤ ያስገመልግማል፤ አፈፃፀሙ የማሻሻልበትን ዘዴ ይቀይሳል፤ ተግባራዊ ያደርጋል፤
 • ሌሎች ከበላይ ኃላፊው የሚሰጡ ተመሳሳይ ተግባራትን ያከናውናል፡፡

Contact Info

ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ከንፋስ ስልክ የሙያ ትምህርት ቤት አጠገብ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ፣ ፖ.ሳ.ቁ  5686