Home » About Us » Quality Control Management

Quality Control Management

 • ከኮሚሽኑ ስትራቴጂክ ዕቅድ በመነሳት የዳይሬክቶሬቱን ዓመታዊ ዕቅድና በጀት ያዘጋጃል፤ ለሚመለከተዉ አካል ያቀርባል፤ ሲፀድቅም ለፈጻሚዎች ያስተዋዉቃል፣ በስራ ላይ እንዲዉል ያደርጋል፤ አፈጻጸሙን ይከታተላል፣ ይገመግማል፤
 • ለዳይሬክቶሬቱ ስራ የሚያስፈልጉትን የሰዉ ሀይል፣ የማቴሪያል፣ የቴክኖሎጂ፣ የንብረትና ሌሎች ልዩ ልዩ ግብአቶች እንዲሟላ ያደርጋል፤ በአግባቡ ስራ ላይ መዋላቸዉን ያረጋግጣል፤
 • የዳይሬክቶሬቱን ስራ ለማከናወን ምቹ የስራ ሁኔታዎች እንዲፈጠሩ ያደርጋል፤ በስሩ ያሉ ፈጻሚዎችን ይመራል፤ ይቆጣጠራል፤ የፈጻሚዎችን የስራ አፈጻጸም ይገመግማል፤ የፈጻሚዎች አፈጻጸም እንዲሻሻል አስፈላጊዉን ስልጠና እንዲያገኙና ተሞክሮዎችን እንዲቀስሙ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፤
 • ለተለያዩ አደጋዎች ምላሽና ለምግብ ዋስትና ኘሮግራም በግዥም ሆነ በዕርዳታ ወደ መጋዘን የሚገባ እህል በተሰጠው የጥራት እስፔሲፊኬሽን መሠረት ጥራቱ የተጠበቀ መሆኑን ያረጋግጣል፣
 • በስራ ላይ ያሉ የእህል/የምግብ የጥራት ደረጃ መስፈርቶችን ከወቅቱ ሀገራዊ  አሰራር ጋር የተጣጣመ መሆኑን ያረጋግጣል፤ እንደአስፈላጊነቱም መስፈርቶቹን እንደአዲስ በማዘጋጀት ወይም በመከለስ ለኮምሽነሩ ያቀርባል፤ ሲፀድቁም ተግባራዊ ያደርጋል፤
 • ለተለያዩ አደጋዎች ምላሽና ለምግብ ዋስትና ኘሮግራም ድጋፍ ጥቅም ላይ ሰለሚውሉ እህልና እህል ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች አያያዝ፣ የጥራት ቁጥጥርና የእህል ደህንነት ህክምና አደራረግን በተመለከተ ከሚመለከታቸው የሥራ ሂደቶች ጋር በመሆን ገለጻና ተግባራዊ ትምህርት ይሰጣል፤ሙያዊ ድጋፍ ያደርጋል፣እህልና እህል ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶችን ለማከማቸት የተገነቡ አዳዲስ ስትራተጂክ መጋዘኖች ለክምችት አመቺ መሆናቸውን ከሌሎች ባለሙያዎች ጋር በመሆን ያረጋግጣል፣
 • የምግብ ክምችትን ከብልሽትና ከብክነት ለመከላከል የሚያስችል የጥራት ቁጥጥር ሥራ አመራር ሥርአት ይዘረጋል፤ የአስተዳደር ዘዴዎችን ይቀይሳል፤  ሲፀድቅም ተግባራዊ ያደርጋል፤
 • የምግብ ጥራት ቁጥጥር ስራ አመራርን የተመለከቱ የጥናት ዉጤቶችን ይገመግማል፤ ያፀድቃል ወይም እንዲፀድቅ ያደርጋል፤ ተግባር ላይ እንዲዉሉ በማድረግ  አፈጻጸማቸዉን ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤
 • ሥራ ላይ ለዋሉ የጥናት ዉጤቶች የአሰራር መመሪያና ማኑዋል እንዲዘጋጅ ያደርጋል፤ ይገመግማል፤ ያፀድቃል፤ ተግባራዊነቱን ይከታተላል፤
 • የእህል ጥራት ቁጥጥር ስራ አመራርን በየወቅቱ ለማሻሻል በሀገር ዉስጥ ወይም በዉጭ ሀገር ምርጥ ተሞክሮዎች እንዲለዩና እንዲቀመሩ ያደርጋል፤ ይገመግማል፤ ተግባራዊ እንዲሆኑ ያደርጋል፤ ይቆጣጠራል፡፡
 • እህል ወደ ክምችት ሲገባና ከክምችቱ ሲወጣ የተደረጉ የጥራት ምርመራ መረጃዎች፣ የጥራት ቁጥጥር ስራ አመራርን ለመተግበር ስራ ላይ የዋሉ የተለያዩ ዶክሜንቶች፣ ክምችቱን ከተባይ ጥቃት ለመጠበቅ የተከናወኑ የእህል ህክምና መረጃዎችና ሌሎች ተዛማጅ መረጃዎች ወቅታዊና ተደራሽ ሆነዉ የሚያዙበትን ሥርዓት ይዘረጋል፤ ተግባራዊነቱን ያረጋግጣል፡፡
 • ለምግብ ጥራት መመርመሪያ አገልግሎት ስራ ላይ የሚዉሉ የተለያዩ መሳሪያዎችና የክምችቱን ደህንነት ለመጠበቅ የሚያገለግሉ ጸረ-ተባይ መድሀኒቶች፣ የህክምና ሸራዎችና ተያያዥ መሳሪያዎች፣ የማከማቻ መጋዘኖች፣ የአሰራር ዘይቤዎችን  /methods/ ሀገራዊ ወይም አለም-አቀፍ ስታንዳርድ መስፈርትን ያሟሉ መሆናቸዉን ያረጋግጣል፤ ክፍተቶች ሲያጋጥሙም እንዲስተካከል ለሚመለከተዉ የስራ ክፍል ያሳዉቃል፤ ዉጤቱን ይከታተላል፡፡
 • የዳይሬክቶሬቱን ዓላማ ለማሳካት የሥራ ዘርፎችን ቅንጅትና ትስስር በማጠናከር የሥራ ግንኙነት ያመቻቻል፤ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ይሰራል፡፡
 • የዳይሬክቶሬቱን የአሰራር ችግሮች በመለየት የአሰራር ማሻሻያ ጥናቶች እንዲከናወኑ ያደርጋል፤ ግብረመልስ ይሰጣል፤ ተግባራዊ እንዲሆኑ ያደርጋል፤
 • ለስራ ክፍሉ የሚያስፈልጉ የሰው ሀብትና ቋሚና አላቂ እቃዎች እንዲሁም ለስራ አስፈላጊ የሆኑ ሌሎች መገልገያ መሳሪያዎች እንዲሟሉ ያደርጋል፤
 • የለውጥ መሳሪያዎችን በሥራ ክፍሉ ተግባራዊ ያደርጋል፤
 • በሥራ ክፍሉ የሚገኙ ሰራተኞችን አፈፃፀም በየወቅቱ ለማሻሻል የሥራ አፈፃፀም ምዘና ስርዓትን ተግባራዊ ያደርጋል፤
 • ከሰው ኃብት ሥራ አመራር ዳይሬክቶሬት ጋር በመተባበር የዳይሬክቶሬቱ ሰራተኞችን አቅም የማጎልበት ስራ ይሰራል፤
 • የዳይሬክቶሬቱን ዕቅድ አፈፃፀም በየወቅቱ ሪፖርት በማዘጋጀት ለዕቅድ፣ ለውጥና መልም አስተዳደር ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ያቀርባል፤ ይገመግማል፤ ያስገመልግማል፤ አፈፃፀሙ የማሻሻልበትን ዘዴ ይቀይሳል፤ ተግባራዊ ያደርጋል፤
 • ሌሎች ከበላይ ኃላፊው የሚሰጡ ተመሳሳይ ተግባራትን ያከናውናል፡፡

Contact Info

ቀጥታ መስመር: +251- 115529534

አድራሻ፤ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ከንፋስ ስልክ የሙያ ትምህርት ቤት አጠገብ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ