Home » About Us » Transformation & Good Governance

Transformation & Good Governance

 • የኮሚሽኑን የሥራ እንቅሥቃሴ ጠንካራና ደካማ ጎኖችን ለይቶ  በመገምገም ጠንካራ ጎኖችን ይበልጥ አጠናክሮ  ለመቀጠል ደካማ ጎኖችን ለመቀነስና ከተቻለም ለማስወገድ በየዓመቱ የተቋማዊ ብቃት ግምገማ እንዲካሄድ ያደርጋል ፣የግምገማውን ውጤት በማቀነባበርና በመተንተን ለኮሚሽነሩ ያቀርባል፣
 • የተቋማዊ ለውጥን ቀጣይነትን የሚያረጋግጡ አዳዲስ የአሠራር ስርዓቶች በማጥናት፣ ምርጥተሞክሮዎችን በመቀመር በኮሚሽኑ ጠቃሚ የሆኑትን ተግባራዊ ያደርጋል፣
 • የተቋሙን አመታዊ የለውጥና መልካም አስተዳደር እቅድ በማዘጋጀት ለስራ ክፍሉ ባለሙያዎች እንዲሁም ለኮሚሽኑ ሰራተኞች በማቅረብ ውይይት እንዲደረግበትና ይሁንታን እንዲያገኝ ያደርጋል፡፡
 • የብሔራዊ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ስትራቴጂክ እቅድ ሰነድን መነሻ በማድረግ የኮሚሽኑን መሠረታዊ የሥራ ሂደት ለውጥና የውጤት ተኮር ትግበራ ይከታተላል፣ የግምገም ሥራዎችን በማከናወን የመሥሪያ ቤቱን የሩብ ዓመት አፈጻጸም ውጤት ሪፖርት አዘጋጅቶ ያቀርባል፡፡
 • የኮሚሽኑን የለውጥ ሥራ አመራር እንቅስቃሴና የአገልግሎት አሠጣጥ ለግብ ስኬት ምቹ የሚያደረገውን የውጤት ተኮር አተገባበር ለመገምገም የሚያስችል ስልት ይዘረጋል፣
 • የልማት ሠራዊት ግንባታ፣ አደረጃጀትና አተገባበር በማኑዋሉ መሰረት ስለመሆኑ ተከታታይ ክትትልና ድጋፍ የደርጋል፤
 • የደንበኞች ውጤት ላይ ተመስርቶ በተቋማዊ ልማትና በችግር ፈችነት ላይ ያተኮሩ ጥናቶችን  ያጠናል፡፡ስልጠናና የምክር አገልግሎት ይሰጣል፡፡
 • የተቋሙን የሠራተኞችን የሥራ አፈጻጸም ውጤት  ይገመግማል፣ ውጤታማ የሆኑ ሰራተኞችን ያበረታታል፣ የአቅም ክፍተትያለባቸውን ሰራተኞች በመለየት ልዩ ድጋፍ እንዲያገኙ ያደርጋል፣
 • ወቅታዊ ዕቅድና የዕቅድ አፈጻጸም  ሪፖርቶች ዝግጅት በታቀደላቸው ጊዜ ተጠናቀው ለሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላትና ተጠቃሚዎች እንዲደርሱ  አፈጻጸማቸውን ይከታተላል፣ ይደግፋል፤
 • የመ/ቤቱን የሥራ ባህል ፣የአሠራር ስርዓቶች እና አደረጃጀቱን በየጊዜው ለማሻሻል የሚያስችሉ የለውጥ አጀንዳዎችን ይቀርጻል፣
 • ለኮሚሽኑ ተስማሚ የሆኑ  ዘመናዊ የለውጥ ሥራ አመራርና የአሠራር ማሻሻያ ስልቶች ተለይተው እንዲቀርቡ ያደርጋል፤ መረጃዎች በአውቶሜሽን አንዲደራጁ ያደርጋል፣
 • የልማት ሰራዊት የህዝብና የመንግስት ክንፎችን በመለየት  የትግበራ ትስስር ይፈጥራል፤ የጋራ ዕቅድ  እንዲኖራቸው ያስተባብራል፣ በጋራም ይተገብራል፣
 • በተግባር ላይ እንዲውሉ የተመረጡ የለውጥ መሳሪያዎች አተገባበር ከሁኔታዎች ጋር ተጣጥመው እንዲሰራባቸው ስልት ይቀይሳል፣
 • የአገልግሎት ስታንዳርዶች፣ የስልጠና ሰነዶችና የአፈጻጸም መመሪያዎች እንዲዘጋጁ  ሃሳብ ያቀርባል፣ አብሮ ይሰራል፣ያስተባብራል፣  ጥቅም ላይ መዋላቸውንም ይከታተላል፤
 • የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ስለለውጥ ዓላማዎች እንዲገነዘቡና የህዝብ አገልጋይነት ስሜት እንዲያዳብሩ የአመለካከት ለውጥ እንዲያመጡ ተከታታይነት ያላቸው የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮች እንዲዘጋጁ ተግባራዊ እንዲሆኑ ያደርጋል፣
 • በኮሚሽኑ የሚገኙ የሥራ ዘርፎች በአስቀመጡት ተቋማዊ የለውጥ ግቦች እና እቅድ መሠረት መፈጸማቸውን ይገመግማል፣ ክፍተት ካለው የመፍትሄ አቅጣጫ ያስቀምጣል፣
 • በመልካም አስተዳደር ማስፈንና በኪራይ ሰብሳቢነት ምንጮችንና የማክሰሚያ ስልቶችን በመለየት መልካም የሆነ ሂደትን በማስፈን በኩል ከሚመለከታቸው ከውጭና ከውስጥ አካላት ጋር ጥምረት ይፈጥራል፣ በጋራም ተግባራዊ ያደርጋል፤
 • በተቋማዊ ለውጥ፣ በስራ ክፍሎች አቅም ክፍተት፣ በመልካም አስተዳደር ችግሮችና መንሲኤዎቻቸው ላይ ያተኮሩ ጥናቶችን ያስተባብራል፣ የስልጠናና የምክር አገልግሎቶች በተገቢው መንገድ እንዲከናወኑ ተገቢው ይፈጽማል፣ ያስፈጽማል፤
 • በተቋማዊ ለውጥና ትራንስፎርሜሽን ላይ ያተኮሩ የውይይት፣ የልምድ ልውውጥ ወይም የዕውቀት ሽግግር መድረኮች እንዲዘጋጁ ሃሳብ ያቀርባል፣ የዝግጅቱንና የአፈጻጸሙን ሂደት ይመራል፣ ውጤቱንም ከባለሙያዎች ጋር በጋራ ይገመግማል፤

Contact Info

ቀጥታ መስመር: +251-115584308

አድራሻ፡ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ከንፋስ ስልክ የሙያ ትምህርት ቤት አጠገብ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ፣ ፖ.ሳ.ቁ  5686 ስ.ቁ. 251- 1 524259/524272 ፋክስ 251-01-514788.